ባሕር ዳር: ሚያዝያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ” ወደ ፕሪምዬር ሊግ ለማደግ ወሳኝ የኾነው የደሴ ከተማ እና የሀላባ ከነማ ጨዋታ ዛሬ በሀዋሳ ይካሄዳል።
የምድቡ መሪ ሀላባ ከነማ እና የመድቡ ተከታይ ደሴ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። ጨዋታው 10፡00 ላይ ይካሄዳል።
የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፈው ክለብ ወደ ፕሪምዬር ሊጉ የማደግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
በ35 ነጥብ ሊጉን የሚመራው ሀላባ ከነማ ዛሬ ካሸነፈ አንድ ጨዋታ እየቀረው ወደ ፕሪምዬር ሊጉ ማለፉን ያረጋግጣል።
በ34 ነጥብ የሚከተለው ደሴ ከተማ ካሸነፈ መሪነቱን ይረከባል። ወደ ፕሪምዬር ሊግ ለማለፍም እድሉን በእጁ ያስገባል። ይህ ወሳኝ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።
የቡድኑ ደጋፊዎች በሀዋሳ በመገኘት ተጫዋቾችን እንዲያበረታቱም ክለቡ ጥሪ አቅርቧል።
በምድብ “ሀ” ጋሞ ጨንቻ ወደ ፕሪምዬር ሊጉ ማደጉን ማረጋገጡ ይታወሳል።
በምስጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



