አርሰናል ከቦርንማውዝ- የአብሮ አደግ አሠልጣኞች የዛሬ ፍልሚያ።

0
24

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን ለማንሳት ጥረት እያደረገ ያለው አርሰናል ዛሬ በኤምሬትስ ስታዲየም ቦርንማውዝን ያስተናግዳል።

ጨዋታው ከፉክክሩ ባሻገር የሁለቱ ስፔናውያን አሠልጣኞች የሚካኤል አርቴታ እና አንዶኒ ኢራዮላ ልዩ ትዕይንት ነው። ገና በዘጠኝ ዓመታቸው በአንቲጉኦኮ አካዳሚ ጓደኝነት የጀመሩት ሁለቱ አሠልጣኞች ከ30 ዓመታት በኋላ በዓለማችን ፈታኝ ሊግ ውስጥ በተቃራኒ ቆመዋል።

አርሰናል ያለፉትን አራት ጨዋታዎች በማሸነፍ በሊጉ አናት ላይ ተቀምጦ የነጥብ ልዩነቱን ወደ 12 ለማስፋት ይጫወታል።

ይሁን እንጂ ባለፉት 11 ጨዋታዎች ሽንፈት ያልቀመሰው ቦርንማውዝ ለአርሰናል ከባድ የቤት ሥራ እንደሚኾን ይጠበቃል።

በመድፈኞቹ በኩል ኤቤሬቺ ኤዜ ከጉዳት ሲመለስ፣ የሳካ እና ቲምበር መሰለፍ ግን አጠራጣሪ ኾኗል። ጨዋታውም ቀን 8፡30 ላይ ይካሄዳል።

በሌላ በኩል በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሊቨርፑል የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ተስፋውን ለማለምለም ዛሬ ምሽት 1፡30 ላይ ፉልሀምን ያስተናግዳል። በመርሲሳይዱ ክለብ በኩል አሊሰን ቤከር እና ዋታሩ ኢንዶ በጉዳት የማይሰለፉ ሲኾን ጨዋታው ለሊቨርፑል ወደ ድል የመመለሻ ወሳኝ ፈተና ተደርጎ ተወስዷል።

በሊጉ ዛሬ ሌሎች ጨዋታዎችም ሲደረጉ ብሬንት ፎርድ ኤቨርተንን ሲያስተናግድ በርንለይ ብራይተንን ይጋብዛል። ጨዎታዎቹም በተመሳሳይ ሰዓት ቀን 11፡00 ላይ ነው የሚካሄዱት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here