ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር አጓጊ ኾኖ እየቀጠለ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ” 19ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ረፋድ 3:00 ላይ በሃዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም አዲስ አበባ ከተማን እና ከደሴ ከተማ አገናኝቷል። ጨዋታው በደሴ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
አዲስ አበባ ከተማን 2ለ1 ያሸነፈው ደሴ ከተማ ከመሪው ሀላባ ከተማ ጋር ያለውን ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል።
ቅዱስ ተስፋዬ በ5ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ አዲስ አበባ ከተማ ቀዳሚ ኾኖ ነበር። ቢላል ገመዳ በ13ኛው እና በጋሻው ክንዴ በ29ኛው ደቂቃ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ደሴ ከተማ ውጤቱን ቀልብሶ አሸንፏል።
የምድቡ መሪ ሀላባ ከተማ በ35 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ሲገኝ ደሴ ከተማ በ34 ነጥብ ይከተላል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



