ደሴ ከተማ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል።

0
18
ባሕርዳር፡ ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በከፍተኛ ሊግ 19ኛ ሳምንት በምድብ “ለ” ሁለተኛ ቀን ጨዋታ ደሴ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም ጠዋት 3፡00 ላይ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል።
ደሴ ከተማ ወደ ፕሪምየርሊጉ ለማለፍ ያለውን ተስፋ ከፍ የሚያደርግበትን ጨዋታ ነው የሚያደርገው።
የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ በ35 ነጥብ ምድቡን እየመራ የሚገኘውን ሀላባ ከተማን በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ ስለሚከተል እና በቀሪ ጨዋታዎች እርስ በእርስ የሚገናኙ በመኾኑ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የማለፍ ዕድሉን ከፍ ያደርግለታል።
ሀላባ ከተማ ቀደም ሲል በመንጌ ቤኔሻንጉል መሸነፉ እና ከሰሎዳ አደዋ ጋር ያለግብ አቻ ወጥቶ ነጥብ መጋራቱ የክለቡ ወቅታዊ አቋም እየተንሸራተተ ለመኾኑ ማሳያ ነው። ይህ ደግሞ ለደሴ ከተማ መልካም አጋጣሚ ኾኖለታል።
ደሴ ከተማ ዛሬ የሚጫዎተው በምድቡ በ11 ነጥብ ግርጌ ላይ ከሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ጋር በመኾኑ ጨዋታው ይከብደዋል ተብሎ አይጠበቅም።
ደሴ ከተማ ባለፈው ዓመትም ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ዕድሉን አግኝቶ የነበረ ቢኾንም በተከታታይ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ነጥብ በመጣሉ ጉዞው በአጭር መቀጨቱ የሚታዎስ ነው። ዛሬስ ክለቡ ያገኘውን ወርቃማ ዕድል ያባክናል ወይስ በአግባቡ ይጠቀምበታል የሚለው ቀሪ ጨዋታዎችን አጓጊ አድርጓቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here