ሚኬል አርቴታ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ ተብለው ተመረጡ።

0
8

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአርሰናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጋቢት ወር ምርጥ አሠልጣኝ ተብለው ተመርጠዋል።

አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ አርሰናል በመጋቢት ወር ያደረጋቸውን የሊግ ጨዋታዎች ሁሉንም በድል እንዲወጣ ማድረጋቸውን ያሁ ስፖርት ዘግቧል።

አሠልጣኙ አርሰናልን ለእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ እያቀረቡት መኾኑንም ገልጿል። አሠልጣኙ በወሩ ሦስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን አድርገው ሦስቱንም አሸንፈዋል።

አርሰናል ከተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ በዘጠኝ ነጥቦች ርቆ ሊጉን እየመራ ነው።

የኒውካስትል ዩናይትዱ አጥቂ ዊሊያም ኦሱላ ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ያስቆጠራት ግብ የመጋቢት ወር የወሩ ምርጥ ግብ ኾና ተመርጣለች።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here