በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ተጠባባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
6

 

ባሕርዳር፡ መጋቢት 25/2018 ዓ.ም(አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ከሀገራት ጨዋታ መልስ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል።

ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ደግሞ የጣና ሞገዶቹ እና አጼዎቹ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ቀን 7፡00 ላይ ባሕርዳር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ በሚያደርጉት ጨዋታ የሳምንቱ የሊጉ ጨዋታ ይጀመራል።

የደረጃ ለውጥ የሚያስከትለው ይህ ጨዋታ ብርቱ ፉክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ 9፡ዐዐ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ጨዋታ ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ ነው። ከአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መልቀቅ በኋላ የውጤት መራቅ ያጋጠመው ፋሲል ከነማ በዛሬው ጨዋታ የሚያስመዘግበው ውጤት ይጠበቃል።

በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ሸገር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ 10፡00 በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ ይጫወታሉ። የመቻል የሽረ ምድረገነት ጨዋታ ምሽት 12፡00 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲዬም ይካሄዳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here