ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለዓለም ዋንጫ አለፈች።

0
16
ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጃማይካ ጋር የተጫወተው አፍሪካዊቷ ሀገር ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለዓለም ዋንጫ አልፋለች።
ቢቢሲ በዘገባው ዴሞክራቲክ ኮንጎ ይሄን ድል ለዓመታት ስትጠብቀው ኖራለች ብሏል። ድሉ ከእግር ኳስ ጨዋታ በላይ እንደኾነም አንስቷል።
ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ እ.አ.አ በ1974 ዓ.ም በዓለም ዋንጫው የተሳተፈችው የቀድሞዋ ዛየር የአሁኗ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ52 ዓመታት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫው ተሳትፎ ተመልሳለች።
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢንተርኮንቲኔንታል ጨዋታ ጃማይካን ለ1ለ0 አሸንፋ ነው ወደ ዓለም ዋንጫው ማለፏን ያረጋገጠችው። የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች አክሲል ቱዋንዛቤ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሮ ሀገሩን ወደ ዓለም ዋንጫው አስጉዟታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here