የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ የሰዓት መሻሻያ ተደረገበት።

0
54
ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደርጋል።
ጨዋታው ምሽት 12፡00 ላይ ሊከናወን ቀጠሮ ተይዞለት ነበር።
አሁን በወጣ መረጃ የኢትዮጵያ እና የሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ጨዋታ የሰዓት ሽግሽግ ተደርጎበት ምሽት 1፡00 ላይ እንደሚጀምር ካፍ ማስታወቁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ገልጿል።
ጨዋታው በሞሮኮ ኤል-አብዲ ስታዲየም ይደረጋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመልሱን ጨዋታ በድሬዳዋ ስታዲየም የሚያደርግ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here