ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጉዳት ምክንያት ከጨዋታ ርቆ የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።
ክለቡ አል ናስር ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ልምምድ መመለሱን አስታውቋል። በሳዑዲ ፕሮ ሊግ አልናስር ከአል ፋያህ ጋር ባደረገው ጨዋታ የጡንቻ ጉዳት ያጋጠመው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለሳምንት ከሜዳ ርቆ ቆይቷል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጉዳት ምክንያት ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ መደረጉም ይታወሳል። ትናንት አመሻሽ ላይ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ልምምድ መመለሱን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።
ክለቡ አል ናስርም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ልምምድ ሢሠራ የሚያሳይ ምስል በማጋራት አምበሉ ተመልሷል ብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



