የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ይጫወታል።

0
71
ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደርጋል።
በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን ትገጥማለች። ጨዋታው በሞሮኮ ኤል-አብዲ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ ይደረጋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ጨዋታ ሙሉ ቀይ ማልያ ለብሶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።
የሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ቢጫ ማልያ በጥቁር ቁምጣ ለብሶ እንደሚገባ ተገልጿል።
ከቀናት በፊት ወደ ሞሮኮ ያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሞሮኮ ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመልሱን ጨዋታ በድሬዳዋ ስታዲየም የሚያደርግ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here