በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
49
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ዛሬ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል የባርሴሎና እና የኒውካስትል ዩናይትድ ጨዋታ አንደኛው ነው። በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 1ለ1 በኾለ አቻ ውጤት ያጠናቀቁት ክለቦቹ ዛሬ ምሽት ወደ ሩብ ፍጻሜው የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 2:45 ይካሄዳል።
በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የሚጫወተው ባርሴሎና ጨዋታውን የማሽነፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቶት። ባርሴሎና በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ያለውን ጥንካሬ ዛሬም እንደሚያሳይ ይጠበቃል።
በመጀመሪያ ጨዋታ ወደ ቱርክ ተጉዞ በጋላታሰራይ 1ለ0 የተሸነፈው ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የመልሱን ጨዋታ ያደርጋል። ምሽት 5:00 በሚደረገው ጨዋታ ሊቨርፑል ውጤቱን ቀልብሶ እንደሚያልፍ ይጠበቃል።
በሌሎች የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ በመጀመሪያው ዙር ከሜዳው ውጭ አታላንታን 6ለ1 ያሸነፈው ባየርሙኒክ በሜዳው ምሽት 5:00 ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
ወደ ስፔን ተጉዞ በአትሌቲኮ ማድሪድ 5ለ2 የተሸነፈው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የመልሱን ጨዋታ ይጫወታል።
በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ቶተንሃም ውጤቱን ቀልብሶ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ከሦስት በላይ ግቦችን ማግባት ይጠበቅበታል።
ጨዋታው ምሽት 5፡00 ይካሄዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here