የሴኔጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን የካፍን ውሳኔ ተቃወመ።

0
39
ባሕር ዳር: መጋቢት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የ2025 የአፍሪካ ዋንጫን ከሴኔጋል ነጥቆ ለሞሮኮ መስጠቱን ትናንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የካፍ ውሳኔ በመላው ዓለም በሚገኙ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ኾኗል። የካፍ የይግባኝ ሰሚ ቦርድ ሴኔጋል በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ያልተገባ ስነ ምግባር ማሳየቷን እና ሕግ መጣሷን ምክንያት በማድረግ ነው ዋንጫውን እንደነጠቃት ያስታወቀው።
ለካፍ ውሳኔ መልስ የሰጠው የሴኔጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ውሳኔው ኢ ፍትሐዊ መኾኑን ገልጿል። የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህንን ኢ ፍትሐዊ፣ ታይቶ የማይታወቅ እና ተቀባይነት የሌለው ውሳኔ ያወግዛል ብሏል። ውሳኔው በአፍሪካ እግር ኳስ ላይ ጥላ የሚያጥል መኾኑንም አስታውቀዋል።
የሴኔጋልን መብት እና የሴኔጋል እግር ኳስ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ፌዴሬሽኑ በተቻለ ፍጥነት ለዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ፍርድ ቤት (CAS) ይግባኝ እንደሚያቀርብም ገልጿል።
ፌደሬሽኑ ለታማኝነት እና ለስፖርት ፍትሕ እሴቶች ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንደሚያረጋግጥም አስታውቋል። በሂደቱ የሚከሰቱ ለውጦችን ለሕዝብ እንደሚያሳውቅም ገልጿል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ትናንት ምሽት ላይ ዋንጫውን ከሴኔጋል ነጥቆ ለሞሮኮ መስጠቱን በመግለጫ እንዳሳወቀ የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ከደጋፊዎች ጋር ደስታውን ሲገልጽ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አጋርቶ ነበር።
በታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here