ባሕር ዳር፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም(አሚኮ)30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
በዚህ ሳምንት ከሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል ዛሬ ምሽት 2:30 በስታንፎርድ ብሪጅ የሚካሄደው የቼልሲ እና የኒውካስትል ዩናይትድ ጨዋታ አንደኛው ነው።
አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቼልሲ ማሸነፍ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። ኒውካስትልም ድል ማድረግ ከ12ኛ ደረጃ እስከ ደረጃው አጋማሽ ያሳድገዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ይኽንን ወሳኝ ጨዋታ በራዲዮ እና ኤፍ ኤም ጣቢያቹ በቀጥታ ያስተላልፋል።
እርስዎም 8200 ላይ የውጤት ግምትዎን መልእክት በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



