በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
71

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም(አሚኮ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። የሊጉ መሪ አርሰናል በሜዳው እና በደጋፊው በፊት ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል። የእያንዳንዱ ጨዋታ እንደ ፍጻሜ በሚቆጠርበት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ አርሰናል ዛሬ ካሸነፈ መሪነቱን ያጠናክራል።

ጨዋታው ምሽት 2:30 ይካሄዳል። አርሰናል ከኤቨርተን ጋር ባደረጋቸው የመጨረሻዎቹ ስድስት የፕሪምዬር ሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም። አራት ጨዋታዎችን አሸንፎ በሁለቱ ደግሞ ነጥብ መጋራቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ለዋንጫ ቅድመ ግምት ያለው አርሰናል እያሳየው በሚገኘው የአጨዋወት ዘይቤ እየተተቸ መኾኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

በፕሪምዬር ሊጉ ለዋንጫ ከሚደረገው ፉክክር ባሻገር የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ይዞ ለማጠናቀቅ የሚደረገው ፉክክርም ብርቱ ነው። የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ይዞ ለማጠናቀቅ ከሚፎካከሩ ክለቦች መካከል ደግሞ ቸልሲ አንደኛው ነው።

ቸልሲ ዛሬ በሜዳው ኒውካስትል ዩናይትድን ይጋብዛል። ጨዋታው ምሽት 2:30 ይካሄዳል። ቸልሲ ኒውካስትን በሜዳው ከጋበዘባቸው ያለፉት 12 ጨዋታዎች በአንዱም አልተሸነፈም። 11 ጊዜ ሲያሸንፍ በአንደኛው ጨዋታ ደግሞ አቻ ተለያይቷል። የዛሬው ጨዋታስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገብበት ይኾን የሚለው ይጠበቃል።

ከአርሰናል ጋር ለዋንጫ የሚፎካከረው ማንቸስተር ሲቲም ዛሬ ጨዋታ አለው። የአርሰናል የጨዋታ ውጤት አይቶ የሚገባው ማንቸስተር ሲቲ ወደ ለንደን ተጉዞ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ምሽት 5:00 ይጫወታል። ባለፉት ጨዋታዎች በዌስትሃም ላይ የበላይነት ያለው ማንቸስተር ሲቲ በዛሬው ጨዋታም እንደሚያሸንፍ ይጠበቃል።

በሌሎች ጨዋታዎች ሰንደርላንድ ከብራይተን እና በርንሌይ ከቦርንማውዝ ምሽት 12:00 ይጫወታሉ።

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here