ስለ ኢትዮጵያዊ አቡበከር ናስር አሠልጣኙ የሰጡት ሀሳብ።

0
331

ባሕርዳር: የካቲት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አሠልጣኝ ሩላኒ ማክዌና በአቡበከር ናስር ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ዙርያ አስተያየት ሰጥተዋል።

ከሳምንታት በፊት የደቡብ አፍሪካው ክለብ ተጨማሪ የውጭ ዜግነት ያለው ተጫዋች ማስፈረሙን ተከትሎ የአቡበከር ናስር ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ መግባቱ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ አሠልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ስለ ተጫዋቹ አኹናዊ ሁኔታ በሰጡት አስተያየት የተጫዋቹ ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል። ለእግር ኳስ ሂወቱ አደጋ የኾነ ጉዳት እንዳጋጠመው የገለፁት አሠልጣኙ ክለቡ ይፋዊ መግለጫ ይሰጥበታል ብለው እንደሚያስቡም ተናግረዋል።

” ክለቡ መግለጫ ይሰጣል ብዬ አስባለሁ፤ ነገር ከፓይሬትስ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ያጋጠመው በጣም ከባድ እና የተወሳሰበ ጉዳት ነው። “ገና አላገገመም ግን ለማገገም በጣም እየታገለ ነው። ይህም ትንሽ አሳዛኝ ነው፤ ምክንያቱም ይህ አይነት ኹኔታ ለእግር ኳስ ሂወቱ የሚያሰጋ ነው” ብለዋል።

አሠልጣኙ አክለውም ተጫዋቹ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውና በቅርቡ ይመለሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። “እኛ ልንሰጠው የምንችለውን ሁሉ ድጋፍ ያስፈልገዋል፤ በርግጥ ተጫዋቾቹን የሚንከባከብ ጥሩ ክለብ ውስጥ ነው ያለው። በቅርቡ እናየዋለን ብለንም ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ ከመራ በኋላ የቁርጭምጭሚትና የጉልበት ጉዳት ጨምሮ ሦስት ከባባድ ጉዳቶች የገጠሙት አቡበከር በቀጣይ ጊዜያት ከክለቡ ጋር ያለውን ቆይታ ይወሰናል ተብሎ ይገመታል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here