ባሕር ዳር፡ መጋቢት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
ሁለት የጣሊያን ክለቦች ቦሎኛ እና ሮማ የሚገናኙበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። በቅርብ ጊዜ በተገናኙባቸው የእርስ በእርስ ጨዋታዎች ቦሎኛ የተሻለ የማሸነፍ ንጻሬ አለው።
ሮማ ከዚህ ቀደም ከሀገሩ ክለቦች ጋር በአውሮፓ መድረክ ሦስት ጊዜ ተገናኝቶ በኢንተር ሚላን እና በፊዮሬንቲና ተሽንፏል። ኤሲ ሚላንን ደግሞ አሸንፏል። የዛሬውን ጨዋታ ያሸንፍ ይኾን ? የሚለው በጉጉት ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 2:45 ይካሄዳል።
ሊል እና አስቶን ቪላ የሚገናኙበት የዩሮፓ ሊግ ጨዋታም ተጠባቂ ነው።
አስቶን ቪላ በታሪኩ በፈረንሳይ ምድር ባደረጋቸው ስድስት አህጉራዊ ጨዋታዎች ድል ቀንቶት አያውቅም። በዛሬው ጨዋታ አሸንፎ አዲስ ታሪክ ይጽፋል ? ወይስ በፈረንሳይ ምድር ድጋሜ ይሸነፋል የሚለው ይጠበቃል።
አሁን ላይ ለሊል እየተጫወተ የሚገኘው የቀድሞው የአርሰናል እና ቼልሲ አጥቂ ኦሊቪዬር ጅሩድ ከአስቶን ቪላ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ስምንት ጨዋታዎች 10 ግቦችን በማስቆጠር አስደናቂ ታሪክ አለው። ጨዋታው ምሽት 2:45 ይካሄዳል።
ፓናቲናይኮስ ከሪያል ቤቲስ እና ስቱትጋርት ከፖርቶ በተመሳሳይ 2፡45 ይጫዎታሉ።
ሴልታ ቪጎ ከኦሊምፒክ ሊዮን፣ ፈረንክቫሮስ ከስፖርቲንግ ብራጋ፣ ጌንክ ከፍራይበርግ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከሚድጄይልላንድ ምሽት 5፡00 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



