አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ አደረጉ።

0
53

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

አሠልጣኙ ጥሪ ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርጋቸው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣርያ ጨዋታዎች ነው።

✍️ በግብ ጠባቂ :- አቡበክር ኑራ፣ ፍሬው ጌታሁን
እና ሰይድ ሃብታሙ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

✍️በተከላካይ መስመር:- ያለምብርሃን ይግዛው፣ አስራት ቱንጆ፣ ያሬድ ካሳዬ፣ አብዱሰላም የሱፍ፣ ያሬድ ባዬ፣ ራሚኬል ጀምስ፣ ምኞት ደበበ እና ግሩም ሀጎስ ተመርጠዋል።

✍️በአማካይ ስፍራ:- ሃብታሙ ተከስተ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ብሩክ እንዳለ፣ ብዙዓየሁ ሰይፈ፣ ወገኔ ገዛኸኝ እና ቢኒያም አይተን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ናቸው።

✍️ በአጥቂ መስመር:- ቸርነት ጉግሳ፣ መስፈን ታፈሰ፣ አቡበክር ሳኒ፣ ካቤ ብዙነህ፣ አቤል ያለው እና ከነአን ማርክነህ ተመርጠዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here