በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ይቀጥላሉ።

0
61

 

ባሕርዳር፡ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም(አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ አራት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በሁሉም ውድድሮች ለዋንጫ እየተፎካከረ የሚገኘው አርሰናል ወደ ጀርመን ተጉዞ ከባየርን ሊቨርኩሰን ጋር ይጫወታል። ሁሉንም የሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች አሸንፎ ለጥሎ ማለፍ የደረሰው አርሰናል ዛሬ የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።ጨዋታው ምሽት 2:45 ይካሄዳል።

ማንቸስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ከዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል አንደኛው ነው። በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በተደጋጋሚ እየተገናኙ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 5፡00 ይካሄዳል።

ፓሪስ ሴንት ጄርሜን እና ቸልሲ የሚያደርጉት ጨዋታም ሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ ነው። የባለፈው ዓመት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ፒኤስጂ ባለፈው የውድድር ዘመን በእንግሊዝ ክለቦች ላይ ያሳየውን የበላይነት ዛሬም ይደግመው ይኾን የሚለው ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 5፡00 ይካሄዳል።

በሌላ ጨዋታ ቦዶ ጊልሜት ከስፓርቲንግ ሊዝበን ጋር ይገናኛሉ። ጨዋታው ምሽት 5፡00 ይደረጋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here