በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
47

 

ባሕር ዳር፡ የካቲት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ 22ኛ ሳምንት ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ባሕር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ሁለቱ ክለቦች በ21ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ መሸነፋቸው ይታወሳል። ባሕርዳር ከተማ ዛሬ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል። ጨዋታው ቀን 9:00 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲዬም ይካሄዳል።

ባሕር ዳር ከተማ በሊጉ እስካሁን 21ጨዋታዎችን አድርጎ በ27 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከኾነ ደረጃውን የማሻሻል እድል ይኖረዋል።

ታጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በ26 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።

ፋሲል ከነማ ዛሬ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል። 21ጨዋታዎችን አድርጎ 33 ነጥብ የሠበሠበው ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ ጨዋታ 39 ነጥብ ሠብሥቦ አንደኛ ደረጃ ከተቀመጠው ሲዳማ ቡና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት ስቧል።

ጨዋታው ቀን 9፡00 በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋል።

በሌሎች ጨዋታዎች አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በሀዋሳ ዩኒበርሲቲ ስታዲየም እና ወላይታ ዲቻ ከሀዋሳ ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ 12፡00 ይጫወታሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here