ፋሲል ከነማ ከውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ዛሬ ይጫወታል።

0
16
ባሕር ዳር፡ የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ ዛሬ ሲቀጥል በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ፋሲል ከነማ ከውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ምሽት 12፡ዐዐ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በ20ኛው የሊጉ ሳምንት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የተገናኘው ፋሲል ከነማ 3ለ1 መሸነፉ የሚታወስ ሲኾን የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎ ወደ ድል ሥነልቦና ለመመለስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል።
በሊጉ በ33 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ደረጃውን አስጠብቆ ለመቆየት ያስችለዋል።
ተጋጣሚው ውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በ20ኛ የሊጉ ሳምንት ጨዋታ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለግብ በመለያየት ያለውን ወቅታዊ ጥንካሬ አሳይቷል። በዚህም ለፋሲል ከነማ ቀላል እንደማይኾንለት ይጠበቃል።
ይሁን እንጅ ውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሊጉ በ18 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክለብ በመኾኑ ለፋሲል ከነማ የተሻለ የጨዋታ ሥነልቦና ይዞ ለመግባት እንደሚያግዘው ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here