ባሕር ዳር፡ የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ ዛሬ ሲቀጥል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባሕር ዳር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ምሽት12፡ዐዐ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በ20ኛው የሊጉ ሳምንት ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የተገናኘው ባሕር ዳር ከተማ 1ለ0 ጨዋታውን አሸንፍ ወደ ማሸነፍ ስነልቦና ተመልሷል።
ባሕር ዳር ከተማወች ዛሬ ታዲያ በዚህ ጥሩ ሁኔታ ላይ ሁነው ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት።
ባሕር ዳር ከተማ በ27 ነጥብ ስምንተኛ ኾኖ ነው የሚጫዎተው።
ተጋጣሚው አርባምንጭ ከተማ በበኩሉ ባለፈው ሳምንት ከነገሌ አርሲ ጋር 1ለ1 በመለያየት ነጥብ የተጋራ ቡድን ነው።
ቡድኑ በሊጉ በ13 ነጥብ እና በ13 የግብ ዕዳ ያለበት ቡድን ከመኾኑም በላይ በሊጉ ግርጌ ላይ ነው የተቀመጠው።
ክለቡ ይህን ጨዋታ ቢያሸንፍም እንኳን የደረጃ ለውጥ አያደርግም።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



