የአውሮፓ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታዎች ውጤት፦

0
22
ባሕር ዳር፡ የካቲት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምሽት ላይ በተካሄዱ የአውሮፓ ሊግ 16ቱን ለመቀላቀል በተደረገ ጨዋታ ፈሪንካቫሮስ በድምር ውጤት ሉዶጎሬትስን 3ለ2 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
ሊል ሬድ ስታር ቤልግሬድን በድምር ውጤት 2ለ1 አሸንፎ 16ቱን ተቀላቅሏል።
ስቱትጋርት ሴልቲክን በድምር ውጤ 4ለ2 በማሸነፍ ነው ወደ ጥሎ ማለፍ ጨዋታው የተቀላቀለው።
ፓናቲኒያኮስ ደግሞ ከቪክቶሪያ ፕልዜን ጋር በድምር ውጤት 3ለ3 በመለያየታቸው የግሪኩ ክለብ በመለያ ምት 4ለ3 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግሯል።
ቦሎኛ ብራን በደርሶ መልስ ጨዋታ ውጤት 2ለ0 አሸንፎ የጥሎ ማለፍ ጨዋታው ላይ ደርሷል።
ሴልታ ቪጎ ፓኦክን በደርሶ መልስ 3ለ1 በኾነ ውጤት አሸንፎ 16ቱ ውስጥ መግባት ችሏል።
ኖቲንግሃም ፎረስት ፌነርባቼን በደርሶ መልስ 4ለ2 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግሯል።
ጌንክ ደግሞ ዲናሞ ዛግሬብን በደርሶ መልስ ጨዋታ 6ለ4 በኾነ ውጤት አሸንፎ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here