ፖርቱጋል ላይ የተነሳው ውዝግብ ሳይቋጭ ስፔን ላይ የተፋጠጡት ሪልማድሪድ እና ቤኔፊካ

0
31

 

ባሕር ዳር: የካቲት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቤኔፊካ ረያል ማድሪድን አስተናግዶ በሜዳው 1ለ0 መሸነፉ ይታወሳል። የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ዛሬ ስፔን ላይ ይጠበቃል።

ጨዋታውን ማን አሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር ያልፋል ከሚለው በላይ ከሳምንት በፊት ፖርቱጋል ላይ ተከስቷል የተባለው ዘረኝነት አሁንም እሳቱ አልበረደም። በቪኒሽየስ ላይ የዘረኝነት ጥቃት ፈጽሟል የተባለው ፕሪስቲያኒ ለጊዜው በአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር የአንድ ጨዋታ እገዳ ተጥሎበታል። ይህን ተከትሎ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም።

ነገር ግን ተጫዋቹ ወደ ስፔን ተጉዞ ቤርናቦ ላይ ልምምድ እየሠራ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቹ ስሜን ያጠፉትን ቪኒሸስን እና ምባፔን እከሳለሁ፤ ንጹህ ነኝ ብሏል።

በሌላ ወገን የማድሪድ ደጋፊዎች በሜዳው ዙሪያ ዘረኝነትን የሚኮንኑ እና ቪኒሼስን የሚያበረቱ ባነሮችን አስቀምጠዋል። ጨዋታው በዚህ ግለት ውስጥ ኾኖ ምሽት 5:00 ቤርናቦ ላይ ይካሄዳል።

በሪያል ማድሪድ በኩል ኪሊያን ምባፔ በጉዳት ምክንያት በጨዋታው እንደማይሰለፍ ተረጋግጧል። የጨዋታ እገዳ የተጣለበት ፕሪስቲያኒ ደግሞ በቤኔፊካ በበኩል በጨዋታው አይሰለፍም።

በሌሎች ጨዋታዎች አታላንታ በዶርትሙንድ የደረሰበትን የ2ለ0 ሽንፈት ለመቀልበስ በሜዳው ዶርትሙንድን ይገጥማል። ከሜዳው ውጭ ሞናኮን 3ለ2 የረታው ፒኤስጅ ሞናኮን፣ ሳምንት 5ለ2 የተረታው ጁቬንቱስ ጋላታሳራይን የሚጋብዙበት ጨዋታም ምሽት ይጠበቃሉ።

ዘጋቢ፦ አስማማው አማረ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here