በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
27

 

ባሕር ዳር፡በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ አራት ወሳኝ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ይካሄዳሉ።

75 ሺህ 817 ተመልካች በሚይዘው በግዙፉ በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ስታዲየም ምሽት 5:00 ኢንተር ሚላን ከቦዶ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ኾኗል።

የኖርዌዩ ቦዶ አምና በዮሮፖ ሊግ ጨዋታዎች እስከ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰ ጠንካራ ቡድን ነው።

ዘንድሮ ደግሞ በአውሮፖ ሻምዮንስ ሊግ ውድድር ማንቸስተር ሲቲን፣ አትሌቲኮ ማድሪድን እና የጣልያኑ ኢንተር ሚላንን በማሸነፍ አስደናቂ አቋሙ እያሳየ ይገኛል፡፡

ተጋጣሚው ኢንተር ሚላን በሴሪኤው 64 ነጥብ በመሠብሠብ እየመራ ይገኛል። ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር የቅድመ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ወደ ኖርዌይ አምርቶ በቦዶ 3ለ1 መረታቱ ይታወሳል።

ኢንተር ሚላን ወደ ቀጣዩ ጨዋታ ለማለፍ ዛሬ በቦዶ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል። ለማለፍም በሦስት ግብ ልዩነት ማሸነፍ ይኖርበታል።

ጨዋታው ምሽት 5:00 የሚጀምረው ጨዋታ ምላሹን ይሰጠናል።

ሌሎች ጨዋታዎችም ምሽት ላይ ይካሄዳሉ። በዚህም መሠረት በመጀመሪያው ዙር ሦስት አቻ የተለያዩት አትሌቲኮ ማድሪድ እና ክለብ ብሩዥ ምሽት 2:45 ይጫወታሉ።

ምሽት 5:00 ደግሞ በመጀመሪያው ዙር ኦሎምፒያኮስን 2ለ0 ድል ያደረገው ባየር ሊቨርኩሰን በሜዳው ምሽት 5:00 ላይ የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል።

በተመሳሳይ ሰዓት በመጀመሪያው ዙር ከሜዳው ውጭ ካራባግን 6ለ1 ያሸነፈው ኒውካስትል ዩናይትድ ዛሬ በሜዳው ሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም የማለፍ ሰፊ ዕድል ይዞ ይጫወታል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here