ባሕር ዳር: የካቲት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ላሊጋ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር 58 ነጥብ በመሠብሠብ ከመሪው ሪያል ማድሪድ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ በሁለተኛት የተቀመጠው ባርሴሎና ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ከሚገኘው ሌቫንቴ ጋር ምሽት 12:15 ላይ ይጫወታል።
ሪያል ማድሪድ ትናንት በኦሳሱና 2ለ1 መሸነፉ ለባርሴሎና መልካም አጋጣሚን ፈጥሯል። በመኾኑም ዛሬ ባርሴሎና ካሸነፈ ነጥቡን 61 በማድረስ የላሊጋው መሪ መኾን ይችላል።
ተጋጣሚው ሌቫንቴ ጨዋታውን ቢያሸንፍ ለጊዜው ከወራጅ ቀጣናው መውጣት ባይችልም ቀጣይ ጉዞውን ግን ለማሳመር ይረደዋል። ስለኾነም የሁለቱ ቡድኖች ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ተጠብቋል።
በሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች፦
👉 ቀን 9:00 ላይ ጌታፌ ሴቪያ
👉 ምሽት2:30 ላይ ሴልታቪጎ ከማዮርካ
👉 ምሽት 5:00 ላይ ቪያሪያል ከቫሌንሺያ ይጫወታሉ።
ላሊጋውን ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና ቪያሪያል በቅደም ተከተል ይመሩታል።
ማዮርካ፣ ሌቫንቴ እና ሪያል ኦቢይዶ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛሉ ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



