ባሕር ዳር፡ የካቲት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኒውካስትልን በኒኮ ኦሪይሊ ሁለት ግቦች ኒውካስትልን 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል። ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከመሪው አርሰናል ያለውን ልዩነት ወደ ሁለት አጥቧል።
ብራይተን ደግሞ ብሬንትፎርድን 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል
ቸልሲ ከበርንለይ 1ለ1 በመለያየት ነጥብ ተጋርቷል።
አስቶን ቪላ በበኩሉ ከሊድስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በመለያየት ነጥብ ተጋርቷል።
በሌላ በኩል ዌስትሀም ከቦርንማውዝ ያለግብ ተለያይተው ነጥብ ተጋርተዋል።
በተያያዘ ሪያል ማድሪድ ሽንፈት አጋጥሞታል።
በስፔን ላ ሊጋ ኦሳሱና ሪያል ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
የኦሳሱናን ግቦች ቡድሚር እና ጋርሺያ አስቆጥረዋል።
ሪያል ማድሪድን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ቪኒሺየስ ጁኒየር ከመረብ አገናኝቷል።
የሪያል ማድሪድን መሸነፈ ተከትሎ ባርሴሎና የካቲት 15/2018 ዓ.ም የሚያደርገውን ጨዋታ ካሸነፈ የላ ሊጋው መሪ መኾን ይችላል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



