ባሕር ዳር ከተማ ደረጃውን የሚያሻሽልበትን ጨዋታ ዛሬ ያደርጋል።

0
15

 

ባሕር ዳር፡ የካቲት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ 20 ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ሲካሄድ ባሕር ዳር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ቀን 9፡00 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በሊጉ ካደረጋቸው 19 ጨዋታዎች ውስጥ አራት ጨዋታ በማሸነፍ እና በሦሥት ጨዋታ ተሸንፎ 12 ጨዋታ አቻ የተለያየው ባሕርዳር ከተማ 14 ኳሶችን መረብ ላይ አሳርፏል።

በ13 ኳሶች መረቡን ያስደፈረው ባሕር ዳር ከተማ በ24 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ባሕር ዳር ከተማ ዛሬ ወደ ማሸነፍ ለመመለስ ነው ጨዋታውን የሚያደርገው።

ተጋጣሚው ሀድያ ሆሳዕና ካደረጋቸው ጨዋታዎች ስድስቱን አሸንፎ በሰባት በመሸነፍ እና በስድስት ጨዋታ አቻ በመለያየት 24 ነጥብ ይዞ በባሕር ዳር ከተማ በጎል ክፍያ ተበልጦ 10ኛ ደረጃ ያለ ክለብ ነው።

ዛሬ ሁለቱ ክለቦች አንዱ ሌላውን አሸንፎ ደረጃውን ለማሻሻል የሚያደርጉት ጨዋታ በመኾኑ ጥሩ ፉክክር እንደሚኖረው ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here