ሪያል ማድሪድ ከቤንፊካ ጋር ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል።

0
36
ባሕር ዳር: የካቲት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ይካሄዳሉ።
ዛሬ ከሚደረጉ አራት ጨዋታዎች መካከል ቤኔፊካ በሜዳው ስታዲዮ ዳ ሉዛ ስታዲየም ሪያል ማድሪድን የሚጋብዝበት ጨዋታ ልዩ ትኩረት መሳቡን ትልልቅ የመገናኛ ተቋማት እየዘገቡት ይገኛሉ።
ከቀድሞው ቡድናቸውን ጋር የሚጫወቱት አሠልጣኝ ሞሪንሆ ሪያል ማድሪድን ባለፈው ወር በነበረ ጨዋታ 4ለ2 በማሸነፋቸው “ሪያል ማድሪድ ቆስሏል፤ የቆሰለ ንጉሥ ደግሞ እጅግ አደገኛ ነው፤ ይሁንና ጨዋታውን ለማሸነፍ የምናደርገውን እናውቃለን ” ብለዋል።
በጨዋታው ላይ ሪቻርድ ሪዮስ፣ ፍሬድሪክ አውረስነስ እና አሌክሳንደር ባሕ ከውድድሩ ውጪ ኾነዋል። ጆአዎ ቬሎሶ እና ሳሙኤል ሶሬስ የመሰለፋቸው ነገር አጠራጥሯል።
ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ስምንቱን ቡድኖችን ቀጥታ መቀላቀል ያልቻለው በቤኔፊካ በደረሰበት 4ለ2 ሽንፈት ነው፡፡ በመኾኑም ዛሬ የባለፈ ሽንፈቱን ጣፋጭ ድልን ለመጎናጸፍ የሞት ሽረት ጨዋታ ያደርጋል ተብሎ ተጠብቋል።
የሪያል ማድሪዱ አሠልጣኝ አልቫሮ አርቢዮል “የእኛ ትኩረት ምርጡን ጨዋታ ለመጫወት ነው። ተጫዋቾች ግጥሚያውን የመጨረሻ ጨዋታ እንደኾነ አድርገው ተዘጋጅተዋል” ሲሉ ተናግረዋል።
የዛሬው ጨዋታ አስቸጋሪ ቢኾንም ጨዋታውን ለማሸነፍ የምናደርገውን ጠንቅቀን እናውቃለን። እናም ትኩረታችን ጥሩ ውጤት ለማምጣት ቆርጠን ተነስተናል ማለታቸውን ሪያል ማድሪድ ኦፊሻል አስነብቧል።
በማድሪድ በኩል ቤሊንግሃም፣ ኤደር ሚሊታኦ፣ ሮድሪጎ እና ራውል አሴንሲዮ ከጨዋታው ውጪ ይኾናሉ ሲል ፉት ቦል ቱዴይ አስነብቧል
ጨዋታውን ሪያል ማድሪድ ያሸንፋል ሲልም ቅድመ ግምቱን አስፍሯል።
በሌሎች ጨዋታዎች፦
ዶርትሙንድ ከአታላንታ ፣ ሞናኮ ከፓሪስ ሴንት ዠርሜ ምሽት 5:00 ይጫወታሉ።
ምሽት 2:45 ደግሞ ጋላታሳራይ ከዩቬንቱስ የሚጫወቱ ይኾናሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here