ተጠባቂው የናፖሊ እና የሮማ ወሳኝ ጨዋታ

0
42
ባሕር ዳር: የካቲት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጣሊያን ሴሪኤ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከሚደረጉ አምስት ጨዋታዎች መካከል ምሽት 4:45 ላይ ናፖሊ ከሮማ በስታዲዮ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ በውበቱ እና በአጓጊነቱ ተጠባቂ ነው።
ናፖሊ በደረጃ ሰንጠረዡ 49 ነጥብ በመሠብሠብ እና 13 ንጹሕ የግብ ክፍያ በመያዝ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ በጨዋታው ድል ካደረገ ነጥቡን 52 በማድረስ ደረጃውን አጠናክሮ የሚያስጠብቅ ይኾናል።
ሮማ ደግሞ በ46 ነጥብ በመሠብሠብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታውን ካሸነፈ ነጥቡን 49 በማድረስና በግብ ክፍያ በመብለጥ የሦሥተኛነት ደረጃን ከናፖሊ ላይ የሚረከብ ይኾናል።
ቡድኖቹ በነጥብ እና በደረጃ የተቀራረቡ ናቸው። ያሰባሰቧቸው ተጨዋቾች ብቃት፣ የማሸነፍ ሥነ ልቦና፣ ወቅታዊ አቋም እና የደጋፊዎች የማሸነፍ እልህ ተቀራራቢ ነው።
በኤአይስኮር ዶት ኮም መረጃ መሠረት ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2005 ወዲህ በ41 ጨዋታዎች ተገናኝተው ናፖሊ በ16 አሸንፏል።
ሮማም በ15 ጨዋታዎች ሲረታ በ10 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
ናፖሊ በሜዳው እና በደጋፊዎች ፊት ቢጫወትም የዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም ለሮማ ደጋፊዎች ሩቅ አይኾንባቸውም። ሮማዎች ለቡድናቸው የሚደረገውን ሁሉ በማድረግ አይታሙምና ተብሏል።
ይህን ጨዋታ መላው የጣሊያን የእግር ኳስ ቤተሰብ እና የጣልያን ቋንቋ በሚናገሩ ሀገራት የሚገኙ የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ለእግር ኳስ አፍቃሪያን ሁሉ አጓጊ እና ተጠባቂ እንደኾነ ነው አን ኢታሊያ ስፖርት ያስነበበው።
ታዲያ ይህን ወሰኝ ጨዋታ ማን ያሸንፍ ይኾን! ምሽት 4:45ትን በጉጉት መጠበቅ ግድ ይላል።
በሌሎች ጨዋታዎች፦
👉 ቀን 8:30 ላይ ዩዲኔሴ ከሳሱኦሎ
👉ቀን 11: 00 ላይ ክሬሞንሴ ከጄኖዋ
👉 በተመሳሳይ ሰዓት 11:00 ላይ
ፓርማ ከቬሮና
👉 ምሽት2:00 ላይ
ቶሪኖ ከቦሎኛ ይጫዎታሉ።
ሴሪኤውን ኢንተር ሚላን በ61 ነጥብ ይመረዋል። ኤሲ ሚላን በ53 ነጥብ በሁለተኛነት ይከተላል።
ፊዮሬንቲና፣ ሄላስ ቬሮና እና ፒሳ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here