ሊድስ ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ላለመውረድ የሚደረግ ጥረት!

0
6

 

ባሕር ዳር፡ ጥር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሊድስ ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ምሽት 5:00 ይጫወታሉ።

ጨዋታው በሊድስ ዩናይትድ ሜዳ ኢላንድ ሮድ ስታዲየም ይደረጋል።

ሊድስ ዩናይትድ ከ24 ጨዋታዎች በስድስቱ አሸንፎ፣ በስምንቱ አቻ ተለያይቶ፣ በ10 ጨዋታዎች ተሸንፎ በ26 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ቡድኑ ወራጅ ቀጠናው አፋፍ ላይ እንደመቀመጡ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከስጋት እንዲርቅ ያስችለዋል።

የሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ፋርክ “ወሳኝ ተጫዋቾች ጉዳት ላይ ናቸው። ነገር ግን በእነርሱ ምትክ የምናሰልፋቸው ተጫዋቾች የማሸነፍ እልሃቸው እና ወቅታዊ አቋማቸው ጥሩ ነው። እናም ዛሬ የምንጫወተው አለመውረድን እያሰብን በመኾኑ ለማሸነፍ እንጫወታለን” ነው ያሉት።

ተጋጣሚው ኖቲንግሃም ፎሬስት ከ24 ጨዋታዎች በሰባቱ አሸንፎ፣ በአምስቱ አቻ ተለያይቶ፣ በ12 ተሸንፎ 26 ነጥብ በመሰብሰብ 17ኛ ነው።

ቡድኑ ወራጅ ቀጠናው ጠርዝ ላይ እንደመገኘቱ ጨዋታውን ማሸነፍ ተንሸራቶ ወራጅ ቀጠናው ውስጥ እንዳይገባ ያደርገዋል።

አሠልጣኝ ሲያን “ቡድኔ ጥሩ ነው። ጥሩ ቡድን ደግሞ ጥሩ ውጤት ያስመዘግባል ባይ ነኝ” ብለዋል። የተወሰኑ ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፉ አልሸሸጉም።

ሁለቱ ቡድኖች በዘጠኝ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ተገናኝተው ኖቲንግሃም ፎሬስት በአራቱ አሸንፏል። ሊድስ ደግሞ በሦስቱ ድል አድርጓል። በሁለቱ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

ሊድስ እና ኖቲንግሃም በተቀራራቢ ወቅታዊ አቋም እና ወራጅ ቀጠናው አካባቢ በመገኘታቸው የዛሬ ግጥሚያቸው ወሳኝ ነው ተብሏል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here