ካፍ የሥነ ምግባር መተዳደሪያውን ሊያሻሽል ነው

0
6

 

ባሕር ዳር፡ ጥር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ካፍ የሥነ ምግባር መተዳደሪያ ደንቦቹን ለማሻሻል የሚመክር ጉባኤ በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ ከሰሞኑ ሊደረግ ነው።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ (ዶ.ር) ጉባኤው እንደ አውሮፖ አቆጣጠር የካቲት 13/2026 ይካሄዳል ነው ያሉት።

የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በካፍ የዲሲፕሊን ደንቦቹ ዙሪያ ተወያይተው ማሻሻያዎች ይደረጋሉ ብለዋል ዶክተር ሞሴፔ።

ጉባኤው በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ሴኔጋል እና ሞሮኮ የፈጸሙትን የሥነ ምግባር ግድፈት አይነት ዳግም እንዳይከሰት የሚያግዝ የሕግ ማሻሻያ ይደረግበታል ተብሏል።

ተሻሽሎ የሚወጣው ሕግ የሥነ ምግባር ግድፈት የሚፈጽሙ ብሔራዊ ቡድኖች የሚቀጡበትን ሕግ የማያወላዳ ያደርገዋል።

ሌሎችም በ”እኔን ያየህ ተቀጣ” እንዲማሩበት የሚያደርግ የሥነ ምግባር የመተዳደሪያ ደንብ ተሻሽሎ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል ሲል ያስነበበው ጋና ሶከርኔት ዶት ኮም ነው።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here