ባሕር ዳር፡ ጥር 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስል ዩናይትድን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የሲቲን የማሸነፊያ ጎሎች ኦማር ማርሙሽ ሁለቱን እና ራይንደርስ አንዷን አስቆጥረዋል፡፡
ኒውካስልን ከሽንፈት ያላዳነችውን ብቸኛ ጎል አንቶኒ ኢላንጋ አስቆጥሯታል።
በዚህም መሰረት ማንችስተር ሲቲ በዌይምብሌይ ከአርሰናል ጋር የፍጻሜ ተፋላሚነቱን ኤጋግጧል።
በጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



