በኮፓ ኢታሊያ ኢንተር ሚላን ከቶሪኖ ዛሬ ይጫወታሉ።

0
13
ባሕር ዳር: ጥር 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኮፓ ኢታሊያ ጨዋታ ስምንት ቡድኖችን በሩብ ፍጻሜ ማፎካከር ጀምሯል። በዛሬ መርሐ ግብር ምሽት 5:00 ላይ ኢንተር ሚላን ከቶሪኖ ይጫወታሉ።
ጨዋታው በስታዲዮ ብሪያንቴዮ (ዩፓዎር) ስታዲየም ይደረጋል።
ሴሪኤውን በ55 ነጥብ እየመራ የሚገኘው ኢንተር ሚላን በ26 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ቶሪኖ ይጫወታል።
ሁለቱ ቡድኖች በሴሪኤው በ33 ጨዋታዎች ተገናኝተዋል። በ21 ጨዋታዎች ኢንተር ሚላን ሲያሸንፍ ቶሪኖ በአራቱ አሸንፏል። በስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
የሩብ ፍጻሜው በቀጣይ ቀናትም አታላንታ ከጁቬንቱስ፣ ናፖሊ ከኮሞ እንዲሁም ቦሎኛ ከላዚዮ እንደሚጫወቱ ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here