የስፔን ኮፓ ዴል ሬይ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል።

0
25

 

ባሕርዳር፡ ጥር 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ በሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ከአልባሴቴ ጋር ይገናኛሉ።

ጨዋታው በአልባሴቴ ሜዳ ምሽት 5:00 ይካሄዳል።

አልባሴቴ በስፔን ስኳንዳ ዲቪዚዮን (ሁለተኛ የሊግ ደረጃ ማለት ነው) የሚገኝ ቡድን ነው።

አልባሴቴ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኀያሉን ሪያል ማድሪድ 3ለ2 በማሸነፍ ነው ለዛሬው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የበቃው።

አልባሴቴ በ2025/2026 የስኳንዳ ዲቪዚዮን ከ24 ጨዋታዎች 33 ነጥብ በመያዝ 12ኛ ደረጃ ላይ ቢገኝም በኮፓ ዴል ሬይ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ግን ሪያል ማድሪድን ማሸነፉ የቡድኑ ጥንካሬ ማሳያ ነው። ስለኾነም ዛሬ ለባርሴሎናን ከባድ ፈተና ይኾንበታል ተብሎ ተጠብቋል።

ሁለቱ ቡድኖች በታሪካቸው በአራት ጨዋታዎች ተገናኝተው ባርሴሎና በሁሉም ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይ ነው።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here