በጣሊያን እና ስፔን ሊጎች ደረጃ የሚያስቀይሩ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

0
27
ባሕር ዳር: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጣሊያን ሴሪኤ 23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 4:45 ላይ ዩዲኔዜ በሜዳው ሮማን ይጋብዛል።
ሮማ እስካሁን ካደረጋቸው 22 ጨዋታዎች በ14ቱ አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ ተለያይቶ እና በሰባቱ ተሸንፎ 43 ነጥብ በመያዝ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ጨዋታውን ማሸነፉ ሦስተኛ ደረጃን ከናፖሊ እንዲረከብ ያስችለዋል።
ተጋጣሚው ዩዲኔዜ ከ22 ጨዋታዎች 92 ነጥብ በመያዝ 11ኛ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ በጨዋታው ካሸነፈ አንድ ደረጃ የሚያሻሽል ይኾናል። በመኾኑም ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ይኾናል።
ሴሪኤውን ኢንተር ሚላን በ55 ነጥብ ይመረዋል። ኤሲ ሚላን በ47 ነጥብ ይከተላል፤ ናፖሊ በ46 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው።
የስፔን ላሊጋ ደግም በ22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 5:00 ላይ ማሎርካ ከሲቪያ ይጫወታሉ። ማዮርካ ከ21 ጨዋታዎች 21 ነጥብ በመያዝ 18ኛ ላይ ተቀምጧል። ጨዋታውን ማሸነፍ ሦስት ደረጃ ለማሻሻል ያስችላል።
ተጋጣሚው ሲቪያ ደግሞ ከ21 ጨዋታዎች 24 ነጥብ በመሠብሠብ 14ኛ ነው። ጨዋታውን ካሸነፈ ወደ ዘጠነኛ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። በመኾኑም ጨዋታው ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ላሊጋውን ባርሴሎና 55 ነጥብ በመሠብሠብ ይመረዋል። ሪያል ማድሪድ በ54 ነጥብ በሁለተኛነት ሲከተል አትሌቲኮ ማድሪድ በ45 ነጥብ ሦስተኛ ነው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here