በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል የአትሌቲክስ ውድድር ተጀምሯል።

0
34
አዲስ አበባ: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጂማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል የቀጠለ ሲኾን የአትሌቲክስ ውድድር ዛሬ ተጀምሯል።
በውድድሩ መክፈቻ በተደረገ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ወርቂቱ ግርማ ከሰላሌ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ኾና አጠናቃለች። እመቤት ደበበ በተመሳሳይ ከሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ኾና ስትጨርስ ብርቄ ብርሃኔ ደብረ ብርሃን ሦስተኛ ኾና አጠናቃለች።
በ5000 ሜትር ወንዶች የግማሽ ፍፃሜ እና የ100 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ዛሬ የተካሄደ ሲኾን የአትሌቲክስ ውድድር እስከ ጥር 30/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት መካሄዱን ይቀጥላል።
የውድድሩ መካሄድ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማግኘት አስፈላጊ መኾኑ ተገልጿል። የመወዳደሪያ ትራክ ምቹ አለመኾኑ በስፖርኞች እና በባለሙያዎች እንደ ክፍተት ተነስቷል።
በቀጣዮቹ ቀናትም የመወዳደሪያ ትራኩን በማስተካከል በኩል ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በጂማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር አትሌቶች ከ100 እስከ 5000 ሜትር ባሉ ርቀቶች እና በሜዳ ተግባራት ፉክክር ያደርጋሉ።
ፓራሊምፒክ የአትሌቲክስ ዘርፍም የውድድሩ አካል ነው።
በአትሌቲክስ 42 ዩኒቨርሲቲዎች ተሳታፊ መኾናቸውንም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማኅበር ፕሬዝዳንት ዓባይ በላይሁን ለአሚኮ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here