ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ2025/2026 የጥር ወር የተጫዋቾች ዝውውር ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። የተለያዩ ቡድኖችም ተጫዋቾችን እያዛወሩ ይገኛሉ።

የክሪስታል ፓላሱ ዣን ፊሊፕ ማቴታ ኤሲ ሚላንን ለመቀላቀል ተስማምቷል።
ተጫዋቹ ከኤሲ ሚላን ጋር እስከ 2030 የሚያቆየውን ውልም በሰዓታት ውስጥ ይፈርማል ነው የተባለው።

አሠልጣኝ ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ የሚቀጥል ከኾነ ማርከስ ራሽፎርድን የመመለስ ፍላጎት አለው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ፉልሃም ለጆ ዊሎክ ያቀረበውን 20 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ገንዘብ ኒውካስትል ዩናይትድ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል በማለት ያስነበበው ዴይሊ ሜይል ነው።

ሰንደርላንድ የ25 ዓመቱን ፈረንሳዊ የፊት መስመር ተጫዋች ዊልሰን ኢሲዶርን ለናፖሊ ቡድን ለመሸጥ መስማማቱን የዘገበው ካልሲዮመርካቶ ነው።

ሊቨርፑል እና ቼልሲ የ20 ዓመቱን ፈረንሳዊ ተከላካይ ጄረሚ ዣኬትን ለማስፈረም ከሬኔስ ቡድን ጋር እየተነጋገሩ መኾናቸውን ፋብሪዚዮ አስነብቧል።

ቼልሲ ለስትራስቦርግ ቡድን በውሰት ሰጥቶት የነበረውን የ20 ዓመቱን ሴኔጋላዊ ተከላካይ ማማዱ ሳርን መልሶ በመውሰድ ሊያጫውተው መኾኑን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።