ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ!

0
26
ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 10:00 በፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ደግሞ ትልቅ ግምት አግኝቷል።
አጼዎቹ ከ16 ጨዋታዎች በሰባቱ አሸንፈው፤ በስምንቱ አቻ ተለያይተው እና በአንዱ ተሸንፈው በ29 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በፋሲል ከነማ በኩል አምሳሉ ጥላሁን በጉዳት እና አቤነዘር ዮሐንስ በቅጣት በጨዋታው እንደማይሰለፉ ታውቋል።
ፈረሰኞቹ ደግሞ በ17 የሊጉ ጨዋታዎች ስድስቱን አሸንፈዋል። በአምስቱ አቻ እና በስድስቱ ተሸንፈው በ23 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ሀብታሙ ጉልላት በቅጣት ምክንያት በጨዋታው አይሰለፍም ነው የተባለው።
ፋሲል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ ቀደም በ17 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ተገናኝተዋል። አጼዎቹ በስምንት ጨዋታዎች ፈረሰኞቹን በማሸነፍ የበላይ ናቸው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በሰባት ጨዋታ ድል አድርጓል። በሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።
ይህ ተጠባቂ ጨዋታ ቀን10:00 ላይ ይጀምራል።
በሌላ ጨዋታ ቀን 7:00 ላይ አዲስ አበባ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከአርባምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ደግሞ ቀን 9:00 ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫዎታሉ።
በዚሁ ስታዲየም ምሽት12:00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ነገሌ አርሲ ይጫወታሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here