የቀድሞው የአርሰናል እግር ኳስ ተጫዋች ባካሪ ሳኛ ባሕር ዳር ከተማ ገብቷል።

0
24
ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ተጨዋቹ ባካሪ ሳኛ የባሕር ዳር ስታዲዬምን ለመጎብኘት ባሕር ዳር ከተማ ገብቷል።
ከባካሪ ሳኛ በተጨማሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎም ባሕር ዳር ገብተዋል።
እንግዶቹ ሲገቡ የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ለቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው ባካሪ ሳኛ የኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም እንዲያድግ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
የባሕር ዳር ስታዲየም የካፍ እና የፊፋን የጥራት ደረጃዎች በሚያሟላ መልኩ እየተገነባ ነው።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here