እግር ኳስዜናየውጭ ስፖርት አጫጭር የዝውውር ዜናዎች By Walelign Kindie - January 30, 2026 0 52 FacebookTwitterPinterestWhatsApp የተጫዋቾች ዝውውር ጥር 1/2026 ተጀምሮ የካቲት 2/ 2026 ደግሞ ይጠናቀቃል። የዝውውር የጊዜው ከመቋጨቱ በፊት ዛሬን ጨምሮ ባሉት ሦስት ቀናት ቡድኖች ተጫዋቾችን ለማዘዋወር እየሰሩ ይገኛሉ። ከእነዚም መካከል፦ ቼልሲ የ22 ዓመቱን እንግሊዛዊ የሪያል ማድሪድ አማካይ ቤሊንግሃምን ለማስፈረም 150 ሚሊዮን ዩሮ ለማውጣት ማቀዱን ያስነበበው ፊቻጄስ ኢን ስፓኒሽ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ ኮል ፓልመርን በዚህ የዝውውር ወቅት እንደማያስፈረም ሚረር አስነብቧል። አያክስ አምስተርዳም አርሰናል ለኖቲንግሃም ፎረስት በውሰት ሰጥቶት እየተጫወተ የሚገኘውን የ29 ዓመቱን ዩክሬናዊ አማካኝ ኦሌክሳንደር ዚንቼንኮ በ1ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ በቋሚ ውል ለማስፈረም መዘጋጀቱን ፋብሪዚዮ ሮማኖ ነው የዘገበው። ሪያል ማድሪድ ከሚፈልጋቸው አሰልጣኞች አንዱ የአስቶን ቪላው ኡናይ ኤምሪ መኾኑን ስካይ ስፖርት አስነብቧል። ቼልሲ የ20 ዓመቱን ፈረንሳዊ የመሐል ክፍል ተከላካይ ጄረሚ ዣኬትን ለማስፈረም ከሬኔስ ቡድን ጋር ድርድር ላይ መኾኑን የዘገበው ጊቭሚስፖርት ነው። ሪያል ማድሪድ የ26 ዓመቱን የማንቸስተር ዩናይትድ የመስመር ተከላካይ ዲዮጎ ዳሎትን ማስፈረም መፈለጉን ያስነበበው ፊቻጄስ ኢን ስፓኒሽ ነው። ራሂም ስተርሊንግን ለማስፈረም ቶትንሃም በጥብቅ መፈለጉን ቲም ቶክ አስነብቧል። ዩቬንቱስ እና በርንለይም የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው። በሙሉጌታ ሙጨ