ባሕር ዳር: ጥር 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ክሪስታል ፓላስ የዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርሱን አጥቂ ጆርጋን ስትራንድ ላርሰንን ለማስፈረም በመርሕ ደረጃ ተስማምቷል፡፡
ክሪስታል ፓላስ ለዝውውሩ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ማቅረቡን ነው የተነገረው፡፡
የ25 ዓመቱ አጥቂ ዎልቭስን የመልቀቅ ፍላጎት ከፍተኛ መኾኑን ቢቢሲ ስፖርት አስታውሷል፡፡
ተጫዋቹ ዎልቭስን በ2024/ 2025 የውድድር ዘመን ነበር በ30 ሚሊዮን ዩሮ በአምስት ዓመት ውል የተቀላቀለው፡፡
የፓላስ አዲስ አጥቂ ፍለጋ የቡድኑን ወሳኝ አጥቂ ፍሊፕ ማቴታን ወደሌላ ክለብ የመሄድ አይቀሬነትን ያሳያል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



