አጓጊው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ

0
53
ባሕር ዳር: ጥር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በመጀመሪያው ዙር 36 ቡድኖችን አሳትፎ ዛሬ ምሽት 5:00 በሚደረጉ 18 ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።
ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃ የሚይዙ ቡድኖችም በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ይገባሉ።
ከዘጠነኛ እስከ 24ኛ ደረጃን የሚይዙ ቡድኖች ደግሞ በእርስ በእርስ ጨዋታ ጥሎ ማለፉን የሚቀላቀሉ ይኾናል።
እስካሁን አርሰናል እና ባየርን ሙኒክ ከወዲሁ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
ካይራት፣ ስሳቪያፕራግ፣ ቪላሪያል እና አይንትራፍራንክፈርት ከወዲሁ መሰናበታቸው ታውቋል።
ዛሬ ከሦስተኛ እስከ 32ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚያስችላቸውን ነጥብ ለማስመዝገብ ዛሬ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
ዛሬ ምሽት 5:00 የሚደረጉ ጨዋታዎች፦
👉አያክስ ከኦሎምፒያኮስ፣
👉 አትሌቲክ ቢልባኦ ከሰፖርቲንግ ሊዝበን፣
👉 አትሌቲኮ ማድሪድ ከቦዶ፣
👉 ባርሴሎና ከኮፐንሀገን፣
👉 ባየር ሊቨርኩሰን ከቪላሪያል፣
👉 ቤኒፊካ ከሪያል ማድሪድ፣
👉 ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከኢንተር ሚላን፣
👉 ክለብ ብሩዥ ከማርሴል፣
👉 አይንትራ ፍራንክፈርት ከቶተንሀም ሆትስፐር፣
👉 ሊቨርፑል ከካራባግ፣
👉 ማንቸስተር ሲቲ ከጋላታሳራይ፣
👉 ሞናኮ ከጁቬንቱስ፣
👉 ናፖሊ ከቼልሲ፣
👉 ፒኤስቪ ከባየር ሙኒክ፣
👉 ፓፎስ ከስላቪያ ፕራግ፣
👉 ፒኤስጂ ከኒውካስትል ዩናይትድ፣
👉 ዩኒየን ሴንት ጊሎሴ ከአታላንታ ይጫወታሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here