ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የ18 ዓመቱን የባርሴሎና አማካኝ ድሮ ፈርናንዴዝን አስፈርሟል።
ተጫዋቹ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እስከ 2030 ድረስ የሚያቆየውን ውል ነው የፈረመው።
ፒኤስጂ ለፈርናንዴዝ 8 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ ከፍሏል ተብሏል።
የባርሴሎና ፕሬዝዳንት ጆአን ላፖርታ ለካታሎኒያ ሬዲዮ እንደተናገሩት በተጫዋቹ ዝውውር ዙሪያ የነበረው ሁኔታ “የማያስደስት” ነው ብለዋል።
ፈርናንዴዝ እንደ አውሮፖ አቆጣጠር በ2022 ነው የባርሴሎናውን ላ ማሲያ አካዳሚ የተቀላቀለው።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለ



