ሀገራት ትምህርት የሚወስዱበት የሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ።

0
42
ባሕር ዳር፡ ጥር 14/2018ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በሴኔጋል አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ ማግስትም ሀገራት ከሞሮኮ ዝግጅት ትምህርት ሊወሰዱባቸው የሚገቡ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።
የእንግሊዝ የዜና ማሰራጫ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ ባወጣው መረጃ ሞሮኮ በቴሌኮም፣ በትራንስፖርት፣ በኃይል አቅርቦት፣ በባንክ፣ በጸጥታ፣ በሕክምና፣ በመዝናኛ እና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት ረገድ እንከን አልባ ሥራ አከናውናለች ነው ያለው።
ሀገሪቱ ውድድሩን ታሳቢ በማድረግ አራት አዲስ ስታዲየሞችን ገንብታ እና ነባሮቹን አድሳ ያለ እንከን ጨዋታዎችን ማጠናቀቅ መቻሏ አሕጉራዊ ውድድር ለማዘጋጀት ለሚከጅሉ ለሌሎች ሀገራት ትምህርት ሊኾናቸው ይገባል ተብሏል።
ስፖርተኞች እና የስፖርት ቤተሰቦች ሳይጉላሉ የፈለጉትን ጨዋታ በፈለጉት ሰዓት ምቾታቸው ተጠብቆ ይከታተሉ ዘንድ ስታዲየሞቹ ያሉበትን እንደ ታንጊየር፣ ራባት እና ካዛብላንካ የመሳሰሉ ከተሞችን በባቡር ማስተሳሰር ተችሏል።
ምቹ የትራንስፖርት አውታር በመኖሩም “ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ” እንዲሉም ሀገሪቱ ከስፖርት ቱሪዝም ተጠቃሚ ኾናለች።
የቴሌኮም እና የኃይል መሠረተ ልማት የተሟላ በመኾኑ 35ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለዓለም ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ የመገናኛ አውታሮች ተሰማርው ውጤታማ ሥራ ማከናዎናቸውን ቢቢሲ አስታውሷል።
ከመቼውም የአፍሪካ ዋንጫ በላይ በርካታ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነቶች ተፈርመውም ተግባራዊ በመደረጋቸው በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከተገኘው ገቢ በሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ የተገኘው ከ90 በመቶ በላይ መኾኑ ነው የተገለጸው።
ካፍም ከ114 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ነው ቢቢሲ የዘገበው።
በስታዲየሞች እና በዙሪያው የአልኮል መጠጦች፣ ሲጋራ እና መሰል በሰው ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮች የተከለከሉ ነበሩ።
የጥበቃ እና የቁጥጥር ሥራውም በቴክኖሎጂ የታገዘ ስለነበር ጨዋታው በሰላም ተጀምሮ አንድ ወር ሙሉ ዘልቆ በስኬት እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን ሀገራት ሊማሩበት ይገባል ነው የተባለው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here