አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

0
50
ባሕር ዳር፡ ጥር 13/2018ዓ.ም (አሚኮ) የክርሰታል ፓላሱ አጥቂ ዣን ፊሊፕ ማቴታ በዚህ የተጫዋቾች የዝውውር ወቅት መልቀቅ እንደሚፈልግ ለቡድኑ ማሳወቁን ተናግሯል። አስቶንቪላ የተጫዋቹ ፈላጊ ነው።
ቦርንማውዝ ብራዚላዊውን የቫስኮ ዳ ጋማ አጥቂ ራያን ቪቶር ሲምፕሊሲዮን በ30 ነጥብ 6 ሚሊዮን ፓውንድ ለማዘዋወር መቃረቡን አስታውቋል።
አያክስ የ24 ዓመቱን ማኑዌል ኡጋርቴን በውሰት ውል ለማስፈረም መጠየቁ ተሰምቷል። ነገር ግን ዩናይትድ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል።
የቦርሺያ ዶርትሙንድ አሠልጣኝ ኒኮ ኮቫች ቡድንን ለቀው ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የማምራት ጽኑ ዕቅድ እንዳላቸው ተሰምቷል።
ኢንተር ሚላን የአስቶን ቪላውን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየቱን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here