የጥር ወር የሀገራት ደረጃን ስፔን እየመራች ነው።

0
45
ባሕር ዳር: ጥር 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጥር ወር የፊፋ የሀገራት የወንዶች የእግር ኳስ ደረጃ ልየታ መሠረት ሞሮኮ ከአፍሪካ በአንደኝነት ተቀምጣለች፡፡
በፊፋ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ደግሞ በታኅሣሥ ወር ከነበረበት 11ኛ ደረጃ በጥር ወር ወደ ስምንተኛ ከፍ ብሏል፡፡
የ35ኛው አፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮናዋ ሴኔጋል በአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ19ኛ ወደ 12ኛ ደረጃዋን አሻሽላለች፡፡
በአፍሪካ ዋንጫ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ የተሸለመችው ናይጀሪያ በአፍሪካ ሦስተኛ በዓለም 26 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
አልጀሪያ፣ ግብጽ፣ ኮትዲቮር፣ ካሜሩን፣ ቱኒዚያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ማሊ በአፍሪካ በቅደም ተከተል ከአራተኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ መያዛቸውን ፊፋ አስታውቋል፡፡
የዓለም የእግር ኳስ ደረጃ ስፔን በአንደኛነት እየመራቸው ትገኛለች፡፡ አርጀንቲና በሁለተኛነት ትከተላለች፡፡
በፊፋ የጥር ወር የደረጃ ሰንጠረዥ መሠረት ፈረንሳይ ሦስተኛ፣ እንግሊዝ አራተኛ፣ ብራዚል አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ54 ሀገራት መካከል 45ኛ፣ በዓለም ደግሞ 159ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here