በሻምፒዮንስ ሊጉ ወሳኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
61
ባሕር ዳር: ጥር 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሰባተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ከእንግሊዙ አርሰናል ምሽት 5:00 ላይ በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የሊጉ መሪ አርሰናል እስካሁን ያደረጋቸውን ስድስት ጨዋታዎች በማሸነፍ እና 18 ነጥብ በመሠብሠብ በአንደኛነት ይገኛል።
ኢንተር ሚላን ከስድስት ጨዋታዎች በአራቱ አሸንፎ እና በሁለቱ ተሸንፎ 12 ነጥብ በመያዝ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2003 ወዲህ በአራት ጨዋታዎች ተገናኝተው በሁለት- በሁለት ጨዋታዎች አሸንፈዋል። ሁለቱ ቡድኖች የየሀገራቸውን ሊግም በመምራት ላይ ይገኛሉ።
ቡድኖች ካላቸው ወቅታዊ አቋም አኳያ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል።
በሌላ የምሽት 5:00 ጨዋታ የፖርቱጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴንት ዠርሜ የሚጋብዝበት ጨዋታም ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።
10ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ስፖርቲንግ ሊዝበን አሸንፎ ደረጃውን ለማሻሻል ፒኤስጂ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃን ከጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ለመረከብ ስለሚጫወቱ ጨዋታውን አጓጊ አድርጎታል።
ምሽት 2:45 ቦዶ ከማንቸስተር ሲቲ ይጫወታሉ። ቦዶ ከዙር ጨዋታ ላለመውጣት ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ነው የሚጫወቱት።
ከሁሉም ጨዋታዎች አስቀድሞ ምሽት 12:30 ላይ የካዛኪስታኑ ካኢራት ከቤልጀሙ ክለብ ብሩዥ ይጫወታሉ።
በሌሎች የምሽት 5:00 ጨዋታዎች፦
👉 ኮፐንሃገን ከናፖሊ
👉 ኦሎምፒያኮስ ከባየር ሊቨርኩሰን
👉 ሪያል ማድሪድ ከሞኖኮ
👉 ቶትንሃም ከቦሩሲያ ዶርትሙድ
👉 ቪላሪያ ከአያክስ ይጫወታሉ ሲል ያስነበበው ቢቢሲ ነው።
ሻምፒዮንስ ሊጉን አርሰናል ይመራዋል፤ ባየር ሙኒክ ሁለተኛ ነው። ፓሪስ ሴንት ዠርሜ ደግሞ በሦስተኛነት ይከተላል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here