የሴኔጋል አሠልጣኝ በይፋ ይቅርታ ጠየቁ።

0
60
ባሕር ዳር: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ያልተገባ ባህሪ በማሳየታቸው በፊፋ፣ ካፍ እና በስፖርት ወዳዱ ማኀበረሰብ ተቃውሞ እና ውግዘት የገጠማቸው የሴኔጋል ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ፓፔ ቲያው “በፍጻሜው ጨዋታ ባሳየሁት ያልተገባ ባህሪዬ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለዋል።
የ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊው የሴኔጋል ቡድን ዋና አሠልጣኝ ፓፔ ቲያው የዕለቱ ዋና ዳኛ የሰጡትን በቫር የታገዘ ውሳኔ ተከትሎ በሴኔጋል ቡድን በኩል ለተነሳው እሰጥ አገባ ብሎም ተጫዋች ከሜዳ እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገቢ አለመኾኑን አምነዋል።
“ሳላንሰላስል ተጫዋቾቼን ከሜዳው እንዲወጡ ማድረጌ ስህተት መኾኑን አምኛለሁ፤ እናም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ነው ያሉት።
አሠልጣኙ ወደፊት ለእፍርት አልባ የጨዋታ መርሆዎች እና ለአፍሪካ እግር ኳስ በታማኝነት እና በቁርጠኝነት አሠራለሁ ማለታቸውን ካፍ ኦን ላይን አስነብቧል።
አሠልጣኝ ቲያው ካፍ ከሚወሰነው ቅጣት ባለፈ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በሚዘጋጀው የ2026ቱ የዓለም የወንዶች እግር ኳስ ዋንጫ የሴኔጋልን ብሔራዊ ቡድን እንዳይመሩ የሚያደርግ እገዳ ከፊፋ ሊጠብቃቸው ይችላል ነው የተባለው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here