ባሕር ዳር: ጥር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በፈረንሳይ ሊግ አንድ 18ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 5:00 ላይ ፓሪስ ሴንት ዠርሜ ከሊል ጋር በፓርክ ዴስ ፍራንስ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ፓሪስ ሴንት ዠርሜ በሊጉ 17 ጨዋታዎችን አድርጎ በ12ቱ ሲያሸንፍ በሦስቱ አቻ ተለያይቷል። በሁለቱ ተሸንፎ እና 39 ነጥብ በመሠብሠብም በሁለተኛነት ደረጃ ተቀምጧል።
ፒኤስጅ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ነጥቡን 42 በማድረስ መሪ መኾን ይችላል።
ተጋጣሚው ሊል ከ17 ጨዋታዎች በ10 አሸንፎ፣ በሁለቱ አቻ ተለያይቶ በአምስቱ ተሸንፎ እና 32 ነጥብ ይዞ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ ድል ካደረገ ደረጃውን ወደ ሦስት ከፍ ያደርጋል። ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ51 ጨዋታዎች ተገናኝተው ፓሪስ ሴንት ዠርሜ በ29 ጨዋታዎች አሸንፏል።
ሊል በስምንት ጨዎታዎች ነው ማሸነፍ የቻለው። በ14 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
በሌላ የምሽት ጨዋታ 3:00 ላይ ሞናኮ ከሎሬንት ይገናኛሉ።
ሊጉን ሌንስ በመምራት ላይ ነው። ፒኤስጂ በሁለተኛነት እና ማርሴል በሦስተኛነት ይከተላሉ ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



