ባሕር ዳር ከተማ ዛሬ የደረጃ ለውጥ የሚያደርግበትን ጨዋታ ያደርጋል።

0
50
ባሕር ዳር: ጥር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 15ኛው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ሲጀመር ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል 10፡00 ባሕር ዳር ከተማ ከመቀለ 70 እንደርታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የጣና ሞገዶቹ በፕሪምየር ሊጉ በየጊዜው በገጠማቸው የውጤት ቀውስ ውስጥ ቢቆዩም በ14ኛው የሊጉ ጨዋታ መልሰው ከድል ጋር ተገናኝተዋል።
መቻልን 2ለ1 በመርታት ወደ ድል የተመለሱት እና የሞራል ጥንካሬ ያገኙት የጣና ሞገዶቹ ዛሬ ደግሞ ከመቀለ 70 አንደርታ ጋር ያለባቸውን ጨዋታ ለማሸነፍ እና የድል ግስጋሴአቸውን ለማስቀጠል ይጫወታሉ።
ባሕር ዳር ከተማ በሊጉ በ19 ነጥብ እና በአንድ የግብ ክፍያ ዘጠነኛ ጀረጃ ላይ ነው የሚገኘው። የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ደግሞ ደረጃውን በብዙ ማሻሻል የሚችልበት ነው።
ተጋጣሚው መቀለ 70 አንደርታ በ12 ነጥብ በ18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቡድን ነው።
ቡድኑ በ14ኛ ሳምንት በሊጉ ከነበረው የሽንፈት ሂደት ወጥቶ ሸገር ከተማ ጋር አቻ መለያየቱ ለዛሬው ጨዋታ ጥሩ የሞራል ስንቅ ይኾነዋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ለጣና ሞገዶቹም አስቸጋሪ እንደሚኾን ነው የሚጠበቀው።
በሌላ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ከውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲ ጋር 9፡00 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here